Skip to main content

አፍሪካ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት አጋጥሟታል

በአኅጉሪቱ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት ማጋጠሙን የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል፡፡


የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት፣ የሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር መሐመድ ባልሆሲን በሰጡት መግለጫ፥ የመምህራን እጥረቱ በአኅጉሪቱ  አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የተቀመጠውን በትምህርት የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት አኅጉሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል ርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል።

የመምህራን እጥረቱን ለመሙላትና በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ኢንቨስት የሚደረገውን በአግባቡ ለመጠቀምም ጠንካራ ጥረቶች እንደሚያስፈልጉ አስረድተዋል፡፡

በአፍሪካ የመምህራን እጥረትን ለመፍታት፣ የትምህርት መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻል፣ የዘላቂ ልማት ግቦችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ 90 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡

በአፍሪካ ያለው የትምህርት ሥርዓት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

Biology 200 Multiple Questions for Grade 12 Students

Prepared by: Yeshaneh Adimasu (Lecturer at Adama Science and Technology Uuniversity)                                                "Together We Can"  There are #200 multiple questions which is very helpful for all grades, especially for Grade 12 students around every corner of Ethiopia. Th questions are prepared based on the New curriculum from Grade 11 (unit 1-3) and 12 (unit 1&2) and  old curriculum from Grade 9 (Unit 1-3) and 10 (Unit 1)   Those who have interest to access the video lectures from Grade 9, 10, 11, and 12, please visit my YouTube channel "Yeshaneh Tube" on the link: https://www.youtube.com/@yeshanehtube  Further more; If you have any comment and suggestion please write on the comment section  @yeshanehtube  DO carefully !! Good luck  Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives 1. ...

Grade 12 Biology Unit 3: Part 5 (#3): Stages of Cellular respiration (#Kreb_cycle and #ETC)

Grade 12 Biology Unit 3: Energy Transformation (#Part_2): Photosynthesis