Skip to main content

አስመሳይነት ወይስ ደግነት

 "እንቁላሉ ስንት ስንት ነው?" ስትል ጠየቀቻቸው… "አንዱ እንቁላል 4 ብር ነው " ልጄ በማለት መለሱ፣ እማማ… "አምስቱን እንቁላል በ10 ብር ልወሰደው?" ስትል ደግማ ጠየቀቻቸው … "አይጎዳኝም ብለሽ ነው ልጄ?"…በማለት ደከም ባለ ድምፅ መለሱላት… "ከፈለጉ ይሽጡ፣ ካልፈለጉ ግን በቃ መሄዴ ነው" አለች፣ ጠንከር ባለ ድምፅ፣ እማማ ትንሽ አሰቡና ቀና ብለው አይተዋት… "እስካሁን ምንም አልሸጥኩም፣ ባያዋጣኝም እንደ መጀመሪያ ገድ ልቁጠረውና ልሽጥልሽ፣ የፈለግሺውን ያህል እንቁላል በፈለግሺው ዋጋ ውሰጂ…" ሲሉ በደከመ ድምፅ ተናገሩ። ዘንቢሏን አውጥታ 5 እንቁላል መርጣ አስገባች፣ ከበርካታ 100 ብሮች መካከል ነጠላ 10 ብር አውጥታ ወርውራላቸው እየተጣደፈች የሚያምረው ዘመናዊ መኪናዋ ውስጥ ገባች የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷታል። ከጓደኛዋ ጋር ወደ አንድ ዘመናዊ ሬስቶራንት ገብተው የሚፈልጉትን አዘዙ፣ ትንሽ በልተው ብዙ አተረፉ ተዝናኑ። ሂሳቡ ሲመጣ ቢሉ ላይ 1420 ብር ይላል ። ከቦርሳዋ ውስጥ 1500 ብር አውጥታ ሰጠች ። መልሱን ለሪስቶራንቱ ባለቤት ቲፕ እንዲሆነው ነግራው ወጥተው ሄዱ። ይህ ድርጊት ለሬስቶራንቱ ባለቤት አዲስ አይደለም፣ ለእንቁላል ሻጮ ግን አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ነው…

       ※ከድሆችና ከምስኪኖች የምንፈልገውን ለማገኘት የበላይነታችንን ለማሳየት የምንጥረው ለምንድን ነው? የእኛን እርዳታ ለማይፈልጉትስ ቸር ሆነን ለመታየት ለምን እንፈልጋለን?


Comments

Popular posts from this blog

Biology 200 Multiple Questions for Grade 12 Students

Prepared by: Yeshaneh Adimasu (Lecturer at Adama Science and Technology Uuniversity)                                                "Together We Can"  There are #200 multiple questions which is very helpful for all grades, especially for Grade 12 students around every corner of Ethiopia. Th questions are prepared based on the New curriculum from Grade 11 (unit 1-3) and 12 (unit 1&2) and  old curriculum from Grade 9 (Unit 1-3) and 10 (Unit 1)   Those who have interest to access the video lectures from Grade 9, 10, 11, and 12, please visit my YouTube channel "Yeshaneh Tube" on the link: https://www.youtube.com/@yeshanehtube  Further more; If you have any comment and suggestion please write on the comment section  @yeshanehtube  DO carefully !! Good luck  Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives 1. ...

Grade 12 Biology Unit 3: Part 5 (#3): Stages of Cellular respiration (#Kreb_cycle and #ETC)

Grade 12 Biology Unit 3: Energy Transformation (#Part_2): Photosynthesis